
ፕሮጀክት ኢትዮጵያ
ፕሮጄክት ኢትዮጵያ ድርጅት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በዳንግላ አውራጃ ውስጥ የሚገኝና ክገጠር ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ትምህርትን፣ ጤናን እና የምጣኔ ሀብት እርዳታን ይሰጣል።
ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ድርጅት የአካባቢውን ማህበረሰብ የሚያገለግል በአካባቢው የሚመራ የገጠር ልማት ድርጅት ነው። ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር ድርጅቱ ለገጠር ተማሪዎች የትምህርት ዋስትና፣ የተሻለ ቤተሰባዊ ድጋፍ፤ ዘላቂ የግብርና ድጋፍን እና የምጣኔ ሀብት ጥንካሬን ይደግፋል። የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ድርጅት በዳንግላ በሚገኝ አዲስ ቀበሌ ውስጥ ታዳሽ የማይክሮ ብድር ፈንድ ያቋቁማል። ፈንዱ ዝቅተኛ የወለድ መጠን ያለው ሲሆን (አብዛኞቹ አበዳሪ ተቋማት ወለዳቸው 20% ሲሆን የዚህ ፈንድ 5% ብቻ ነው) ለአርሶ አደርዎች፣ በተለይም ለሴቶች፣ ከሌላ ተቋም ብድር ማግኘት ለማይችሉ ያበድራል። እነዚህ አነስተኛ ግን ጉልህ የሆኑ ኢንቨስትመንቶች የሚከፈሉት ከሁለት ዓመት በኋላ ሲሆን በዚህ ጊዜ ሌላ ዙር ብድር ለአዲስ ተቀባዮች ይሰጣል።
የፕሮጀክት ኢትዮጵያ የማይክሮ ብድር ፈንድ ገንዘቡን በዚሁ ቀበሌ ውስጥ ባሚገኝ የቁጠባ እና አበዳሪ ማህበር ወይም ባንክ አስቀምጦ በአካባቢው የሚገኙ የተመረጡ ግለሰቦች ያሉበት ባለአደራ ቦርድ ይተዳደራል። የኢትዮጵያ ንጉሣዊ በጎ አድራጎት ባለአደራ ድርጅት ምይክሮ ብድር ፈንድ ክህሎትን እና እውቀትን ለማስፋት ፣የእርሻ ወጪን ለመቀነስ ፣የሰብል ምርትን ለመጨመር እና ቤተሰቦችን ከድህነት ለማውጣት የሚረዱ የግብርና ማሻሻያዎችን እና ልምዶችን ለመደገፍ ይረዳል።

ስለ ድርጅቱ
ፕሮጀክት ኢትዮጵያ
ፕሮጄክት ኢትዮጵያ ድርጅት በሰሜን ምዕራብ ኢትዮጵያ በዳንግላ አውራጃ ውስጥ የሚገኝ ሲሆን ከገጠር ማህበረሰቦች ጋር በመተባበር ትምህርትን፣ ጤናን እና የምጣኔ ሀብት እርዳታን ይሰጣል።
