አራቱ የባላደራ ድርጅቱ ምሰሶዎች

አራት ቁልፍ የድርጅቱን ምሰሶችን ለመደገፍ ድርጅታችን ድጋፋችሁን ይጠቃል

ትምህርት

የከፍተኛ ትምህርት ዕድሎችን ለማስፋፋት እና ለመደገፍ እንዲያስችሉ የስኮላርሺፕ አቅርቦትን በጥንቃቄ በማመቻቸት ለኢትዮጵያውያን ተማሪዎች የትምህርት እድገት ላይ እንሰራለን። የወደፊት ትውልድ እውቀቱን ለማዳበር የጥራት ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት አሰጣጥ ወሳኝ በመሆኑ በመላ ኢትዮጵያ ለሚገኙ የትምህርት ተቋማት የመሠረተ ልማት እርዳታ በማቅረብ በንቃት እንሳተፋለን።

ሥራ ፈጠራ

በኢትዮጵያ ውስጥ የሥራ ፈጣሪ መንፈስን ለማጠናከር የቆረጥንበት አንዱ አላማችን ነው። በኢትዮጵያ ሥራ ፈጣሪዎችን ለማሳደግ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ በማቅረብ ሥራ ፈጣሪነትን ለማሳደግ እና ለማስፋፋት እንተጋለን። ባለብዙ ግጽ/መልክ የእርዳታ እቅድ አለን። የፋይናንስ ድጋፍ ብቻ ሳይሆን የንግድ እና የጥበብ አሰራሮችና ሀሳቦችን በመደገፍ ወደ አዳዲስ ከፍታዎች ለማምጣት ለመጣር ወስነናል።

ንጉሣዊ ቅርጾችን ማሰባሰብ

አንዱ ዋና ተልዕኮችን በኢትዮጵያ ውስጥ የኢትዮጵያን ንጉሣዊ ቅርጾችን ከሚገኙበት ሰብስቦ ቋሚ የሆነ የንጉሣዊ ታሪካችንን የሚያንጸባርቅ ቤተ መዘክር ለማቋቋም ወስነናል። የአገራችንን ረጅም ንጉሣዊ ታሪክ እና ስርዓት ለመጪው ትውልድ ለማቆየት እና እውቀትን ለማሳደግ፤ በየአገሩ የተበተኑትን ታሪካዊ ቅርጾቻችንን ለሕዝባችን እንዲመለሱ እና እንዲታወቁ እንጥራለን። ይህ ቤተ መዘክር ስለ ኢትዮጵያ ባሕል እና ታሪክ በአገር ውስጥም ሆነ በዓለም አቀፍ ደረጃ የተሻለ ግንዛቤ እንዲኖርና አድናቆትንም ስለሚፈጥር ለሕብረተሰቡ ከፍ ያለ ጥቅም ይሰጣል። ይህንንም ለማድረግ ከዓለም አቀፍ ምሁራን እና የታሪክ ጥበቃ ባለሞዎች ለመስራት ወስነናል።

ምክር

ልዑል ኤርሚያስ ሣኅለ ሥላሴን እና የኢትዮጵያ ዘውድ ምክር ቤትን ለመደገፍ እና ምክር በመስጠት እና አጠቃላይ አስፈላጊ አገልግሎቶችን በመስጠት እንረዳቸዋለን። እነዚህ አገልግሎቶች የሕግ አማካሪን፣ የፋይናንስ ችሎታን እና የፖሊሲ አማካሪን በሀገራዊና በዓለም አቀፍ ደረጃዎች የኢትዮጵያን ዘውድ ቀጣይነት ያለው ስኬትና ተጽዕኖ ለማረጋገጥ የሚያስፈልገውን ሁሉ በማቅረብ አማካሪዎች በመሆን በታላቅ ትህትና እና ደስታ እንቀርባለን።